ሰላም EHPM እንዴት ናችሁ?
ጓደኛችን ወንድምነው ዋለ ጀንበር ይባላል፤ በጥቁር አንበሳ (TASH)
የ 5ተኛ አመት (C2) የህክምና ተማሪ ነው። አሁን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ በእስር ላይ ነው።
የ 5ተኛ አመት (C2) የህክምና ተማሪ ነው። አሁን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ በእስር ላይ ነው።
የምናውቀው ግንቦት 6 ረቡዕ እራት በልቶ ቤተክርስቲያን ከሄደ በኋላ ዶርም አላደረም። መታሰሩን በነጋታው ነው የሰማነው። ልንጠይቀው ብንሄድም በአካል ማግኘት አትችሉም ተብለናል። መርማሪ ፖሊሱም "አርፋችሁ ተማሩ፤ መታሰር ትፈልጋላችሁ እንዴ?" ብሎ መልሶናል። በጣም መልካም ባህሪ ያለው ልጅ ነው። ከታሠረ ዛሬ 31ኛ ቀን ይሞላዋል። ያለምንም ጥፋት ከ1ወር በላይ በእስር ማሰቃየት እንዴት ያለ ጭካኔ ነው?
ጓደኛችን እና ወንድማችን እንዲፈታ ድምፅ እንሁነው።
መብት መጠየቅ ወንጀል አይደለም‼️
የ5ተኛ አመት የህክምና ተማሪውን በአስቸኳይ ፍቱት‼️
የ5ተኛ አመት የህክምና ተማሪውን በአስቸኳይ ፍቱት‼️