የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ችግሮች ወደ ወደተባባሰ ደረጃ ከመድረሱ በፊት አፋጣኝ የሆነ ሃገራዊ ዉይይት
ተደርጎ ጥያቄዎች በዉይይት እንዲፈቱ ጠየቀ።
*********
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በአገሪቱ ሃኪሞች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን አስመልክቶ የሙያ ማህበራትን እና ስፔሻሊቲ ሶሳይቲዎችን ከጤና ሚኒስቴር ጋር ተከታታይ ውይይቶች እንዲያደረጉ በማመቻቸት ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠዉ እና አስቸኳይ መፍትሄ እንዲቀመጥ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የጠቀሰው ማህበሩ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የሚመለከተዉ አካል ትኩረት እንዲሰጥበት ጥሪውን አቅርቧል።

1. ሃኪሞቻችን በሚያነስዋቸው ጥያቄዎች ማለትም የደመወዝ ማነስ፣ የጥቅማጥቅም፣ የስራ ቦታ ደህንነት እንደ ኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ተገቢ መሆኑን የምንቀበል እና ለረጅም ጊዜያት ለሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጉዳዩን ስናቀርብና ስንሰራበት ቆይተናል፡፡ ሆኖም በአሁኑ ሰዓት የጉዳዩ አሳሳቢነት እየጨመረ በመምጣቱ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥበት በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
2. አሁን ያለዉ ሁኔታ ማለትም የጤና አገልግሎቱ እንዲሁም የመማር ማስተማር ሂደቱ በምንም አይነት ደረጃ ቢሆን መስተጓጎሉ ማህበረሰቡን፤የጤና ባለሞያዉን እንዲሁም የጤና ስርአቱን እጅግ ሊጎዳ የሚችል በመሆኑ ማህበሩ ይህ ጉዳይ ወደተባባሰ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የጤና ሚኒስቴርና የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ከባለሙያዎች ጋር በመሆን አፋጣኝ የሆነ ሃገራዊ ዉይይት በየደረጃዉ እንዲያካሂዱ እና ችግሮቹ በዉይይት እንዲፈቱ እንዲደረግ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
3. ሃኪሞቻችን እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ቦታዎች ለእስር እንደተዳረጉ ሰምተናል፡፡ በመሆኑም ባለሞያዎቹ ከእስር እንዲፈቱ እና ወደስራ ገበታቸዉ ተመልሰዉ ለማህበረሰቡ አገልግሎቱን እንዲሰጡ ቢደረግ የተሻለ እንደሆነ እና በዚህ ረገድ የሚመለከታቸዉ አካላት አስፈላጊዉን እገዛ እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡
4. ማህበራችን እንደወትሮው ችግሮችን ለመፍታት እና መፍትሄ ለመስጠት ከጤና ሚኒስቴርም ሆነ ባለድርሻ አካላት በሚያደርጓቸዉ ጥረቶች ላይ ከዚህ ቀደም ሲያደርገዉ እንደነበረዉ ሁሉ አብሮ ለመስራት እና ትብብሩን አጠናክሮ በመቀጠል የመፍትሄዉ አካል ለመሆን ፈቃደኛ እና ዝግጁ እንደሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን ሲል ጥሪ አቅርቧል።
ማለዳ ሚዲያ