Healthcare workers preparing for second strike
Updates
00
D
:
00
H
:
00
M
:
00
S
ዛሬ ከታካሚየ አስታማሚጋ የተደረገ እዉነተኛ ስንብት ።

ዛሬ ከታካሚየ አስታማሚጋ የተደረገ እዉነተኛ ስንብት ።

May 12, 2025
ዛሬ ከታካሚየ አስታማሚጋ የተደረገ እዉነተኛ ስንብት ።
እኔ በአንድ ትልቅ የህክምና ተቋም የምሰራ የ ሁለተኛ አመት ረዚደንት ሀኪም ነኝ። የዛሬ ውሎየን ጨርሸ ስወጣ ላለፉት 10 ቀናት ስከታተላቸው የነበረ ታካሚ አስታማሚ ተከትለውኝ ወጡ እና፣ ምነው ልጄ ዛሬ ፊታችሁ ላይ ሀዘን ይነበባል፣ ደሞ ነገ ጀምራችሁ አትገቡም አሉ ምነው ልጄ አሉኝ በድጋሜ።
እኔም አልኃቸው፣ ቢከፋን ተስፋብንቆርጥ ነው፣ የ 23 አመት ልፋታችን ከኛም አልፋ ስንት ነገር የሚጠብቁብንን ቤተሰቦቻችንን አንገት ቢያስደፋ ነው፣ ይህ ውርደት በኛ እንዲበቃ እና ዳግም በትምህርት በ እውቀት የሚያምን ትውልድ ይፈጠር ዘንድ ነው አልኋቸው።
እሳቸውም እንደው ደሞዛችሁ ስንት ነው አሉኝ።
እኔም መለስሁላቸዉ 11000 ብር ከዚህ ላይ 5 ሺ ብር ለቤት እንከፍላለን በቀረው ቁርስ ሁሌም ሻይ በ ቦንቦሊኖ ነው፡ ምሳ እንጀራ ከበላን ማታ ዳቦ በለውዝ በልተን እናድራለን።
እሳቸውም አሉኝ በሞቴ ልጄ ቤቴ ሙሉ ነዉ ነገ ጀምራችሁ ስራ ስታቆሙ እንዳይርብህ እርጐም ወተትም አለኝ ስልክ ስጠኝ እና ልደውልልህ።
እንደውም ሆድ ብሶኝ ነበር፣ He leaves me on tears at the last day of Work.
Now or Never!
Dont mention my name.