🚩ሁሉም ሰው ለውጥ ይፈልጋል ለውጡን የሚያመጣው ሂደት አካል ግን መሆን አይፈልግም።

ሁሉም ሰው ለውጥ ይፈልጋል ለውጡን የሚያመጣው ሂደት አካል ግን መሆን አይፈልግም።
የኢትዮጵያ የጤና ባለሞያዎች ንቅናቄ መወቅር ከታች እስከላይ ዘርግቷል ወይ?እንቅስቃሴውስ ከባለፈው ተጠናክሯል ወይ?
👆እነዚህ ከብዙዎቻችሁ የሚነሱ ጥያቄዎች ናቸው::
ይህንን ጥያቄ ግን ለመመለስ በቅድሚያ ሁላችንም አራሳችንን  የሚከተሉትን ጥያቄዎች ቀድመን መጠየቅ አለብን።👇
1.እኔ መዋቅሩ እንዲዘረጋ እና የለውጡ ትግል አካል ለመሆን ምን ያክል ሰራሁ::
2. በመጀመሪያው ዙር እንቅስቃሴስ ተሳታፊ ነበርኩ አሁንስ ተስፋ ባለመቁረጥ እታገላለሁ?
3.በመጀመሪያው ዙር እንቅስቃሴስ ተሳታፊ ካልነበርኩስ አሁን ፍርሃትን፤ አድርባይነትንና  ተስፋ መቁረጥን አስወግጄ ከባልደረቦቼ ጋር ልታገል ቆርጫለሁ?
ውድ ባልደረቦቻችን ደጋግመን እንደተናገርነው ይህን እንቅስቃሴ ሁላችንም በባለቤትነት ካልደገፍንና ካልተሳተፍን ዋጋ አይኖረውም::
አዎ! ውጣ ወረዶች አሉ ተስፋ የሚያስቆርጡም ነገሮች እንዲሁ።ግን ለውጥ በአንድ ጀምበር አይመጣም ያለነው 3ኛው ዓለም ላይ ነው ከዛም የባሰ ማለት ይቻላል...ግን
እመኑን ባርነትን በመቻል እና በመለማመድ የበለጠ ትጫናለህ እንጂ ለውጥ አታምጣም።
አሁንም ጠላታችን ማንም አይደለም የገዛ እራሳችን ነን...ለዓመታት የተላመድነው ዝምታ አሁንም ዋጋ እያስከፈለን ነው።
አሁንም ደግመን እንናገራለን ከቴሌግራምና ፌስቡክ ላይክ እና ሼር የዘለለ የእናንተ የነቃ ተሳትፎ ከሌለ እና ከጎናችን ካልቆማችሁ ትግሉ ዋጋ የለውም የእኛም የእናንተም ልፋት መና ነው የሚቀረው::
ደጋግመን ጥሪ እያደረግንላችሁ ነው...መዋቅር የሚኖረው እናንተ ስትሳተፋ ነው!
ለውጥ የሚኖረው ይመለከተኛል ስትሉ ነው!
ያ ከሆነ ደግሞ ይህን እድል አሳልፈን በባርነት ለመኖር  ፈቅደን ሁላችንም የየራሳችንን ምርጫ መውሰድ ነው::
💥ሁሉም ሆስፒታሎች፣ጤና ጣቢያዎች  ላይ የምትሰሩ የማስተባበር አቅሙ ያላችሁ ባለሞያዎች  በዚህ አካውንት @EHPMETH ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ እናናግራችኋለን።
22 days left‼️‼️
የኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች
All Articles