💥💥💥48 Days Left💥💥💥 💥💥💥48 ቀናት ብቻ💥💥💥
እውነት ለመናገር ይህ እንደ ምርጫ ቅስቀሳ ይሄ ስለሚሻልህ ይህን አድርግ የሚባልበት ጉዳይም ወቅትም ላይ አይደለንም። ሁሉም ሰው ኑሮውን እና የሚበጀውን ያውቃል ብለን እናምናለን:: ያላችሁን ሀሳብ ለመናገር ያለው ትንሿ ተነሳሽነት ነገ ለሚጠብቀን ትልቁ ትግል ያለውን ቁርጠኝነት በትንሹም ቢሆን ያሳየል በማለት ነው::
እኛ ባለው ሁኔታ ከእናንተ በተለየ ተጎድተን አይደለም ሁላችንም ጋር ያለውን ብሶት በተደራጀ መልኩ እናቅርብ ብለን እንጂ::
ስለዚህ ጨው ለራስ ስትል ጣፍጥ እንደሚል ብሂሉ ዕጣህን የምትወስንበት ጊዜ አሁን ነው::
ስለዚህ ጨው ለራስ ስትል ጣፍጥ እንደሚል ብሂሉ ዕጣህን የምትወስንበት ጊዜ አሁን ነው::
ይህ ትግል ዳር ደረሰም አልደረሰም ግን ነገ ላለው ህይወትህ አሻራ የምትጥለው አሁን እንደሆነ ልታውቀው ይገባል :: ይህን እድል አሳልፈን ነገ እንደለመድነው እያመረርን ለመቀጠል ግን የመንግስትም የህዝብም መዘባበቻ ከመሆን ውጪ ሌላ ጥቅም እንደሌለው እንውቅ::
እየተናቅን እየተሰደብን ከቀን ሰራተኛ በታች እየተከፈለን ለመቀጠል ቃል እንደገባንም እንቁጠር::
ይበቃል‼️