Healthcare workers preparing for second strike
Updates
00
D
:
00
H
:
00
M
:
00
S
መንግስትም ለውይይት ክፍት ሆኖ ሰራተኞችን ማቀራረብ እና ከስራ የተሰናበቱትን ወደ ስራ እንዲመልሳቸው መንግስት በሚቀበለው ማህበር አማካኝነት በቂ የንቅናቄው ተወካዮች ሲገኙ ለመወያየት የሚቻል እንደሆነ ተግባብተናል።

መንግስትም ለውይይት ክፍት ሆኖ ሰራተኞችን ማቀራረብ እና ከስራ የተሰናበቱትን ወደ ስራ እንዲመልሳቸው መንግስት በሚቀበለው ማህበር አማካኝነት በቂ የንቅናቄው ተወካዮች ሲገኙ ለመወያየት የሚቻል እንደሆነ ተግባብተናል።

June 12, 2025
ዛሬ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር በአፍሪካ ቢሮ የተሳካ ውይይት አድርገናል ።
ዶ/ር ማህሌት ፣ ዶ/ር ሳሙኤል ጨምሮ ሌሎች ከእስር በዋስ እንዲፈቱ ከኢሰማኮ ጋር ስላደረጉት ትብብር ምስጋናን አቅርብያለሁ።
ጤና ባለሙያዎች ከመንግሥት ጋር ለመደራደር የሚያምኑት ማህበር EHPA ቢሆንም በሲቭል ድርጅቶች መዝጋቢ ባለስልጣኑ እንደታገደና ያ ደግሞ ለውይይት አዳጋች እንደሚያደርግ ነገር ግን የጤና ሚንስትር በቂ ተወካዮቹን እንዲገኙ ከፈቀደ ከሎሎች ማህበራት ጋር ውይይት ማካሄድ እንደምቻል ሀሳብ ሰጥችያለሁ። ለምሳሌ ንቅናቄው የራሱ ተደራዳሪ ስላለው ከEMA ጋር መተባበር እንደሚቻል አቅጣጫ በመጠቆም ።
ሰራተኞች በአንድ ማህበር አመኔታ ስለሌላቸው በተናጠል ተደራጅተው ጥያቄ እንደሚያቀርቡ እንጂ ሌላ አጀንዳ እንደሌለ በማስረዳት ።
መንግስትም ለውይይት ክፍት ሆኖ ሰራተኞችን ማቀራረብ እና ከስራ የተሰናበቱትን ወደ ስራ እንዲመልሳቸው መንግስት በሚቀበለው ማህበር አማካኝነት በቂ የንቅናቄው ተወካዮች ሲገኙ ለመወያየት የሚቻል እንደሆነ ተግባብተናል።
በመንግሥት በኩል ጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶ በቅንነት ቢታይ ሰራተኛው የሚፈልገው መሰረታዊ ሰብዓዊ መብት መከበር ፣ ለጥያቄው እውቅና መሰጠት ፣ አስቸኳይ ችግሮችን አሁን መፍታት ሌሎቹን የሀገሪቱን አቅም ባገናዘበ መልኩ በውይይት እንደሚፈታ እንደሚፈልጉ አስረድቻቸዋለሁ ።
በመጨረሻም ለጤና ባለሙያዎች ነጻ የህግ አገልግሎት ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር በትብብር እየሰጠን መቆየታችን የሚታወቅ ሲሆን አብዛኛው ታሳሪ የጤና ባለሞያ የተፈታ ስለሆነ ሁሉንም የህግ ባለሙያዎችን ለማመስገን እፈልጋለሁ ። የቀሩትም በቀጣይ ቀናት የሚፈቱ ይሆናል።
አሸናፊ ዲዲሞስ ( የ EHPM የህግ ክፍል አማካሪ እና አስተባባሪ)