Healthcare workers preparing for second strike
Updates
00
D
:
00
H
:
00
M
:
00
S
የአክሽን ኤድ ጥናት ስለ ጤና ባለሙያዎች ምን ይላል ?  አክሽን ኤድ በአፍሪካ ስድስት ሃገራት በጤና እና ትምህርት ዘርፉ ላይ አካሂዶ ይፋ ባደረገው ጥናት 32 በመቶ (የሀገራቱ አማካኝ) የሚሆኑት የጤና ባለሞያዎች በክፍያ ማነስ ምክንያት ሞያውን ለመልቀቅ በማሰብ ላይ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።

የአክሽን ኤድ ጥናት ስለ ጤና ባለሙያዎች ምን ይላል ? አክሽን ኤድ በአፍሪካ ስድስት ሃገራት በጤና እና ትምህርት ዘርፉ ላይ አካሂዶ ይፋ ባደረገው ጥናት 32 በመቶ (የሀገራቱ አማካኝ) የሚሆኑት የጤና ባለሞያዎች በክፍያ ማነስ ምክንያት ሞያውን ለመልቀቅ በማሰብ ላይ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።

May 21, 2025
የአክሽን ኤድ ጥናት ስለ ጤና ባለሙያዎች ምን ይላል ?
አክሽን ኤድ በአፍሪካ ስድስት ሃገራት በጤና እና ትምህርት ዘርፉ ላይ አካሂዶ ይፋ ባደረገው ጥናት 32 በመቶ (የሀገራቱ አማካኝ) የሚሆኑት የጤና ባለሞያዎች በክፍያ ማነስ ምክንያት ሞያውን ለመልቀቅ በማሰብ ላይ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።
ጥናቱን ፦
🇪🇹 በኢትዮጵያ
🇬🇭 በጋና 
🇰🇪 በኬንያ
🇱🇷 በላይቤሪያ
🇲🇼 በማላዊ
🇳🇬በናይጄሪያ 600 የጤና ባለሙያዎች፣ መምህራንና የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ነው ያካሄደው።
በጥናቱ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን የጤና ባለሙያዎች ምላሽ በሪፖርቱ የሰፈረ ሲሆን የቀረቡት ጥያቄዎችም እ.አ.አ 2020 ጋር በማነጻጸር የቀረቡ ስለመሆናቸው ጠቅሷል።
የኢትዮጵያውያኑ የጤና ባለሞያዎች ምላሽ ምን ይመስላል ?
- ስልሳ አምስት በመቶ (65%) የሚሆኑት የጤና ባለሙያዎች በክፍያ ማነስ ምክንያት ሞያውን ለመልቀቅ በማሰብ ላይ ይገኛሉ። (በጥናቱ ከተሳተፉ 6 ሀገራት ትልቁ ነው)
- መቶ በመቶ (100%) የሚሆኑ የጤና ባለሞያዎች የጤና መገልገያ ቁሶችና መድኃኒት እጥረት መኖሩን ጠቁመዋል። (በጥናቱ ከተሳተፉ 6 ሀገራት ትልቁ ነው)
- ሰባ አምስት በመቶ (75%) የሚሆኑት ለቤተሰቦቻቸው የሚያቀርቡት የምግብ መጠን መቀነሱን አንስተዋል።
- መቶ በመቶ (100%) የሚከፈላቸው ክፍያ አነስተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
- ዘጠና በመቶ (90%) የሚሆኑት የበጀት ቅነሳ እናቶችና ህጻናት ጤና ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል ብለው ያስባሉ።
- ዘጠና አምስት በመቶ (95%) የሚሆኑት ለጤናው ዘርፍ በቂ በጀት አልተመደበም ብለው ያምናሉ።
- ሀምሳ ሶስት በመቶ (53%) የሚሆኑት የታካሚዎች ቁጥር ጨምሯል ብለው ያምናሉ።
- መቶ በመቶ (100%) የሥልጠና ዕድሎች ቀንሰዋል ብለው ያምናሉ።
- ሰባ አምስት በመቶ (75%) የሚሆኑት ሞያቸው የግል ህይወታቸው ላይ (Work-life Balance) ጫና መፍጠሩን ገልጸዋል።
- መቶ በመቶ (100%) የሚሆኑ የጥናቱ ተሳታፊዎች ለጭንቀት የመጋለጥ እድላቸው እየሰፋ መምጣቱን አንስተዋል።
ጥናቱ መንግስታት ውጤት አልባ ከሆነ የIMF የበጀት መቀነስና ዕዳ መክፈል ፖሊሲ ወጥተው ትኩረታቸውን ዜጎቻቸው ላይ ማድረግ አለባቸው ሲል ምክረ-ኃሳብ ያስቀምጣል።
በአቡጃ ስምምነት መሰረት የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት ከአጠቃላይ በጀታቸው 15 በመቶ የሚሆነውን ለጤናው ዘርፍ እንዲያውሉ ይጠበቃል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA