ከዛሬ ጀምሮ ወደን ሳይሆን ተገደን ወደ ሙሉ ለሙሉ የስራ ማቆም አድማ ተሸጋግረናል። በቤታችን እንቆይ። ለጊዜያዊ ችግሮች በፍፁም እጅ እንዳንሰጥ።
መንግስት ለጤና ባለሙያው ክብር ካለውና ለማህበረሰቡ የሚያስብ ከሆነ በየቦታው ከፋፍሎ የሚያከናውን ስብሰባ አቁሞ የታሰሩ ቤተሰቦቻችንን ፈቶ በይፋ የውይይት ጥሪ ማድረግ አለበት። አሁን ጉዳዩን በያዘበት መንገድ የትም ሊደርስ አይችልም።
ውድ የሙያ አጋሮቻችን እንደ እስካሁኑ ሁሉ ያለማወላወል ከEHPM Board የሚወርድላችሁን መመሪያዎች እንደ አላችሁበት ነባራዊ ሁኔታ በፅናት እና በቆራጥነት ተግብሩ። ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ መመልከት ብዙ መስዋዕትነት ያስፍላል። በአቋሙ የፀና ያሸንፋል።
ይህን ጊዜ እርስ በእርሳችን በመረዳዳት እና በመደጋገፍ እናሳልፍ። አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋችሁ በተለይም ከምትኖሩበት ዶርም የተፈናቀላችሁ በውስጥ @EHPMETH ከማስረጃ ጋር አናግሩን።
አንድነት ሀይል ነው!