Healthcare workers preparing for second strike
Updates
00
D
:
00
H
:
00
M
:
00
S
#ጎንደር #ጎደኞቹን ለመጠየቅ የሄደ ሀኪም እና #ፓሊስ

#ጎንደር #ጎደኞቹን ለመጠየቅ የሄደ ሀኪም እና #ፓሊስ

May 16, 2025
#ጎንደር #ጎደኞቹን ለመጠየቅ የሄደ ሀኪም እና #ፓሊስ
ጎንደር ማራኪ ፖሊስ ጣቢያ አንድ ፖሊስ ጋር እያወራን ነበር።ፖሊስ ጣቢያው አካባቢ ጓደኞቼ እስኪመጡልኝ እየጠበቅሁ ለመጠየቅ ሂደን (አስበን የነበረው ማስፈታት ነበር ግን ሰው በአንድ ላይ መምጣት ስላልቻለ)ዘወር ዘወር ስል ወደእኔ መጥቶ ይዞኝ ሄደ እና ማንነቴን ጠየቀኝ የጤና ባለሙያ እንደሆንኩ ነገርኩት እና እዚህ አካባቢ ምን ትሰራለህ ሲለኝ አይ ሚመጡ ጓደኞቼ ነበሩ እነሱን እየጠበቅሁ አልኩት።ከዛ ምን ልታደርጉ ነው ሲለኝ ጓደኞቻችን እና መምህሮቻችንን በሌሊቱ አፍሳችሁ ይዛችሁብን መጥታችሁ አልሁት።
ከዛ እሱም ለምን ታምጻላችሁ አለኝ?ሥራችሁን እየሰራችሁ ለምን አትጠይቁም አለኝ።እኔም ለእናንተ እንድታፍሱላቸው አመጽ አንስተዋል አሏችሁ እንጅ እኛኮ አላመጽንም ረሀብ ልንሞት ነው ድረሱልን ብለን ነው የጠየቅን በእርግጥ ሌሎች ብዙ መሠረታዊ ጥያቄዎች አሉ አልኩት።
ብዬ ጥያቄዎቻችንን እያንዳንዱ ጤና ሥርዓቱ በቦርድ ይመራ ከሚለው ውጭ አስረዳሁት ታዲያ በውይይት ማትፈቱት አለኝ።
ያው ጥያቄው ሰሞኑን የተጠየቀ አይደለም በ2011 ዓ.ም በ2015 ዓ.ም አሁን ደግሞ ለሦስተኛ ጊዜ ነው የተጠየቀው ካሁን በፊት ያሉት ቃል ተገብቶልን አንድም ስላልተፈጸመ በዚህ ዓመት ግን ቦርዱ ከጤና ሚኒስቴር፥ጠቅላይ ሚኒስቴር፥የክልል ጤና ቢሮዎች ጋር እና ሌሎች አጋር አካላት ጋር እንጅ ዞን ወረዳና ቀበሌ ያሉ ማንኛውም አካላት በሚሰበስቡትም ይሁን ቃል በሚገቡት መመለስ አይችልም።ይህም ደግሞ እንደሀገር እንጅ ጎንደር ብቻ አይደለም የተጠየቀ።አዲስ አበባ አለ አለኝ።
አዎ አልኩት።
ሐዋሳ፥መቀሌ፥ባ/ዳር፥
አዳማ፥ጳውሎስ፥ጥቁር አንበሳ፥አሰላ፥ወልቂጤ...ብዬ ግዙፎችን ቲችንግ ሆስፒታል ጠራሁለት።እሱም አይ አሁንኮ ብር የለም ምናምን አለኝ።ከዛ እኔም እኔ ምልህ በ1.8 ትሪሊየን ብር ቤተመንግስት እየተገነባ እንደሆነ ታቃለህ ስለው ኧረ የለም አለኝ።የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት ምን ያህል እንደሆነ ታቃለህ ስለው የለም አለኝ።ስለዚህ ብር አለ የለም ለማለት ይህን ማወቅ አለብህ አልኩት።ግን ቢሆንም ለምን ዘግታችሁ ትወጣላችሁ አለኝ እኛኮ በስድስት ዓመት ውስጥ ሁለት ጊዜ ጠይቀን በውሸት የተታለልን፤በዚህ ዓመት ጥያቄዎቹን ጠይቀን 30 የመልስ ቀናት ሰጥተን ዳባ ልበስ የተባልን፥ከዚያም መንግስት ቢያንስ ቢነቃቃ ብለን የድንገተኛና የጽኑ ህሙማን እንዲሁም የማዋለጃ ክፍል ሳንዘጋ እየሰራን ባለንበት ሰዓት መጥታችሁ እናንተው ከብባችሁ 4 ባለሙያዎችን ከሚሰሩበት ወሰዳችኋቸው እኛም እናንተ ከመጣችሁማ ብለን ትተንላችሁ ወጣን ከዛም ጭራስ ከሚኖሩበት በር እየደበደባችሁ በሌሊቱ ወሰዳችኋቸው።
ከዛ እሱም ግን በእውነት ደሞዛችሁ አንሷችሁ ነው እኛኮ እያብቃቃን እየኖርን ነው አለኝ።ምን ያህል የሚከፈለኝ ይመስልሃል ስለው መቼም ተንደላቃችሁ ነው ምትኖሩ አለኝ።ተው አሁን እንባዬን አታምጣው ብዬ በትንሹ 40,000 አይከፈላችሁም ብሎኝ ቁጭ አለ።ድሮ 6600 ነበር ደሞዝ ሳይጨመር አሁን ግን 7600 ሆኗል ስለው ኩምሽሽ አለ።እኛ ራሱኮ 11500 የተጣራ ይደርሰናል አለኝ።ለዚህ እኮ ነው አድምጡን ዝምብላችሁ አትፈሱን ምንላችሁ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ያላችሁ የጸጥታ አካላት መቼ ነው ከመታዘዝ ወጥታችሁ በራሳችሁ ትክክል ነው አይደለም ምትሉት አልኩት።
እና አሁን ሆስፒታሉ ይሰራል አቁሟል አለኝ ይዛችኋቸው መጣችሁ ማን ነው ሚሰራ።ድንገት እዛ ያሉ ፌደራል ፖሊሶች እያከሙ ካልሆነ አልኩት።
ኃላፊዎች ምን ይላሉ አለኝ እነሱማ የእናንተ ዘመዶች አይደሉ ሚያሳፍሱስ እነሱ አይደሉ ግቡ ብለው ማስጠንቀቂያ በቀን ሁለት ጊዜ እየፃፉ ነው።ግን ግቡ ሚባሉት እዚህ ገብተዋል።
ለማንኛውም እናንተም ጊዜው ቅርብ ስለሆነ እኛን ሳታንገላቱ አቅም ካላችሁ አብራችሁ ጥያቄው ትክክል ነው ብላችሁ ከህዝብ ጋር ጠይቁ።ቢያንስ ግን የውሸታም ካድሬ ተባባሪ ባትሆኑ ለእናንተ ለወደፊት ይጠቅማል ታሪክም ስለሚወቅሳችሁ።የያዛችኋቸውንም ልቀቁልን አልኩት።ከዛ መንግስት ከሰጠ ምላሽ ይስጥ አይ ካለ የሚፈልግ አካል መጥቶ ይክም።ካሁን በኋላ የመንግስት ጤና ሴክተሮች ጥያቄው ካልተመለሰ በማፈስ ሀኪሙን ወደሥራ መልስ እንድምማትችሉ ቅድሚያ እወቁ ስለዚህ ህዝብንና ወደፊት ሚያክማችሁን ባለሙያ ከማንገላታት ያለፈ ምትፈጥሩት አዲስ ነገር አይኖርም።እሱንም መጥታችሁ አይደለም 28 ባለሙያ ሁላችንም አምጥተህ ብታስገባን በፍጹም አይቆምም።
እኛ ቤታችን ለመቀመጥ ፍጹም ወስነናል።እናንተም ነገ ሆስፒታል መምጣታችሁ ስለማይቀር ምታደርጉትን ሁሉ እያሰባችሁ አልኩት።
እኔም እኮ ሀኪም መሆን እፈልግ ነበር ድሮ አልሳካልኝ ብሎ እንጅ አለኝ።እንኳንም አልሆንህ።እኔ ምልህ ልጅህ ጎበዝ ተማሪ እንዲሆን ትፈልጋለህ አልኩት እንዴ በጣም እንጅ አለኝ።ከዛስ ምን ሊሆን ስለው አይ ሀኪም እንዲሆን እፈልግ ነበር ይቅርበት አለኝ።
ለማንኛውም የእኛ እያበቃ ነው ደግሞም እናሸንፋለን።መንግስት እምቢ ካለም የቀን ሥራ ብሰራ የደሞዜን እጥፍ አገኛለሁ ነገ መምህራን ሲነሱም ልታፍሱ ነው?በጭራሽ እንዳታደርጉት ከእኛ እንኳ ካሁን በኋላ ሆስፒታል ብትመጡም ማንንም አታገኙም ግን አትምጡ አልኩት።
ጥያቄው ትክክለኛ ጥያቄ ነው በርቱ ብሎ በል ጠይቅና ሂድ ቤትህን አለኝ።
UoG pedi resident (R1)