#ስጋት እና #ተስፋ 👉 እስከዘላለሙ እንዳይከሽፍ

‎የያዝነው ትልቅ አላማ ነው፣ ጨዋታ ወይም ቀልድ አይደለም።
‎ በተሰጠው የ30 ቀነ-ገደብ ጥያቄያችን ሙሉ በሙሉ የማይመለስ ከሆነ አጠቃላይ የጤና ባለሙያው ወደ ስራ ማቆም ይገባል።

‎ ቀነ-ገደብ የተሰጠው ታካሚ እና ተገልጋዩ ላይ እንግልት ፣ ሞት እንዳይደርስ መንግስት ጊዜ ወስዶ ህዝቡ ሳይቸገር ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ ታስቦበት ነው።

‎በአንዳንዶቻችን የተደቀነው #ስጋት ጤና ባለሙያው ሙሉ በሙሉ ለዚህ የተቀደሰ አላማ ትብብር የማያደርግ ከሆነ ብቻ ነው።

#ተስፋው ግን አንድነት ሀይል ነው ፣ ፍርሀትን ማስወገድ እና በአንድነት መቆም እና መንግስት እስከዛው ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል የሚል ነው።

‎ሁሉም ጤና ባለሙያ መሳተፍ አለበት። ይህ የማይሆን ከሆነና በአንዳንድ ራስ ወዳዶች የአሁኑ ጥያቄ የሚኮላሽ ከሆነ - ጥያቄያችን የሚከሽፈው እስከ ዘለዓለሙ ነው።

‎ከተዘረዘሩትን 12 ጥያቄዎች ውጪ ሌላ አላማ ወይም የፖለቲካ አጀንዳ የለንም!

‎22 days to go
All Articles