በኛ የተማሪነት ዘመን 6ኪሎ ግቢ ዶርም የሚመደቡ የህክምና ተማሪዎች ነበሩ።
የሁለተኛ አመት ተማሪ እያለን የመጀመሪያ አመት ህክምና ተማሪዎች እኛ ግቢ መጡ። ከነሱ መሃል አንዷ ረጅም ፣ ቀይ ፣ ሙስሊም አይኗ የሚያምር ልጅ (በጊዜው የሚያምር አይን እወድ ነበር) ...ሳያት ሳያት ደስ ትለኝ ጀመር።
ከክላስ ሰአት ውጪ ከኬኔዲ ላይብረሪ በቀር የትም አትታይም። ጠዋት ሲከፈት አለች። ። ከሰአት ብሄድም አለች። ማታ እራት በልቼ ስገባ አለች። በእኩለ ሌሊት ብሄድም አላጣትም። አንድ ቀን እስከ ስንት እንደምትቆይ ልየው የሚል እልህ ይዞኝ እስከ 9 ሰአት ቆየሁ። አልቻልኩም። ተሸንፌ ሄድኩ። እንኳን አመታትን ለሳምንት ያን ያህል ማጥናት መቻሌን እጠራጠራለሁ።
ጠዋት ካጠናሁ ከሰአትን ለምዘለው፣ ከሰአት ከደገምኩ ማታ ለምተኛው እኔ አጠናኗ የከረረ ነበር። በገባሁበት ሰአት ካለች አይኗን ልየው ብዬ፣ ከሌለች እስክትመጣ ብዬ ብዙ ማጥናት ለመድኩ። በዚያ ሴሚስተር 3 A+ ኖረኝ። እሷም ወደ ጥቁር አንበሳዋ ተዛወረች።
።
ናትናኤል ይባላል አብሮ አደጌ ነው። የኔ ባች ተማሪ። አስረኛ ክፍል እስክንደርስ ተመሳሳይ አዋዋል ነበረን። 11 ስንገባ የሰፈራችን ልጅ መሆኑን እስክንዘነጋ ድረስ ወጥሮ አንባቢ ሆነ። ከማትሪክ በኋላ ጥቁር አንበሳ ገባ። ናቲ የሰፈራችን ጀግና ነበረ።
እኔ 4 አመት ተምሬ ተመርቄ ባመቱ ናቲን ልጠይቀው ጥቁር አንበሳ ሄድኩ። ከቤተመፅሃፍቱ ህንፃ ያቺ የማውቃት ልጅ ወጣች። እነዚያ ጎላ ጎላ ያሉ አይኖቿ ግን almost ሞጭሙጨው ተከድነው ነበር።
።
በረከት የሚባል ብዙም ሲያጠና የማናየው ጂኒየስ የሰፈራችን ልጅ ነበረ።
በረከት የሚፈልገው አስትሮ ፊዚሲስት መኾን ነበረ።
በረከት ሂሳብና ፊዚክስ ጥያቄ ሲሰራ ስቴፖች እየዘለለ የሚሰራ ቁጥር አዋቂ ነበር።
በረከት ኳስ ሲጫወት እጅግ ጥበበኛ ተጫዋች ነበረ።
የ12ኛ ክፍል ማትሪክ በጣም ምርጥ ውጤት ካመጣ በኋላ ጎንደር ዩንቨርሲቲ ህክምና ክፍል ገባ። ''ለምን ?'' አልኩኝ። የቤተሰብ ግፊት ይመስለኛል።
ሰቅሎ እዛው ዩንቨርሲቲ መምህር ሆነ።
(እኔ ግን የባከነ የፊዚክስና የ እግርኳስ ችሎታው እየታየኝ አዝን ነበረ)።
በርግጥም ሃገራችን
ከሃኪም ይልቅ ለኳስ ተጫዋች የምትመች ናት!
።
አንድ ሰብስፔሻሊስት አጎት አለኝ። ሃገር ውስጥም ውጪም ብዙ የተማረ።
ጳውሎስ የህፃናት ክፍልን መርቷል። አስተምሯል።
ካገር ወጥቶ ሩዋንዳ አገኘሁት።
''ሁለት አመት በሙሉ ጊዜዬ የትምህርት ክፍሉን መራሁ። አስተማርኩ። መኖር ግን አስቸጋሪ ነው። አይበቃኝም?''
ሩዋንዳ ብቻ ሳይሆን፣ ሌሴቶ፣ ቦትስዋና ብዙ ሃኪሞቻችን የፈለሱባት ሃገራት ናቸው። እኔ ባየሁዋቸው ሃገራት ደግሞ ሃኪሞች ብቻ ሳይሆን ለመንግስት ተቀጥረው የሚሰሩ ሁሉ የተሻለ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ናቸው።
።
ከልጅነት ህልማቸው
ከማህበራዊ ህይወታቸው
ከውበት ከማማራቸው
ከሌሎች ችሎታዎቻቸው መስዋዕት አድርገው
ለብዙ አመታት እጅግ ብዙ የደከሙበት ሙያ ....
ባልተመቸ ቦታና ሁኔታ ሁሉ፣ ያለ ቀንና ሰአት ገደብ የሚሰሩበት ሙያ ....
ህልም መኾኑ ቀርቶ ህመም
ስኬት መኾኑ ቀርቶ ቁጭት
የሚፈለግ መኾኑ ቀርቶ የሚያስንቅ ሲኾን አያሳዝንም?
እነሱን አይና የማገኛቸውን ህፃናት በርትታችሁ ተማሩ ማለት ያቅተኛል።
''የሚለፋ ሰው እንዴት ለመኖር ይቸገራል?'' የሚለው የሃኪሞች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሰራተኛ ጥያቄ ነው መሆን ያለበት። ተመጣጣኝ ክፍያ፣ ምቹ የስራ ከባቢ፣ የጤና ሽፋን (የሚያክምበት ቦታ በነፃ መታከም የማይችል ሃኪም ቢመረው ይገርማል?)፣ ሰርቶ የማደግ፣ የትራንስፖርት፣ የመኖሪያ ቤት ጥያቄዎች፣ የመደራጀትና የመደራደር መብት፣ በሹመኛ ካድሬ ሳይሆን በባለሙያ የመመራት ጥያቄ ወዘተ
የሁሉም ሰራተኛ መብት ነው።
ሃኪሞቻችንን የሚያስኮበልሉ ሃገራት ከኛ ብዙ በኢኮኖሚ የተሻሉ ሆነው አይደለም። ቅድሚያ የሚሰጠውን በማወቃቸው እንጂ።
የባለሙያዎቻችን ጥያቄ ዛሬ መነሳት የጀመሩም አይደሉም። ጥያቄዎቻቸውን ፖለቲካዊ መልክ ከመስጠትና በጉልበት ከማፈን መልስ መስጠት የተሻለው ነው።
# ከሃገሬ የጤና ባለሙያዎች ጎን እቆማለሁ!
(ፎቶ የጥቁር አንበሳ ሃኪሞች ተቃውሞ)
Taken From Haileleul Aph Facebook page
https://web.facebook.com/haileleul.aph