የተከበራችሁ ውድ የኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች በሙሉ
እኛ ይህን የጤና ባለሞያውን የዳቦ የህልውና ጥያቄ እየመራን የምንገኝ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተውጣጣን ጤና ባለሞያዎች ወደዚህ እንቅስቃሴ ስንገባ ሊደርሱብን የሚችሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ነቅሰን በማውጣትና እነዚህንም ችግሮች ለሙያችን ክብር እና ለህልውና ጥያቄያችን ስንል ሙሉ ለሙሉ ለመቀበል አምነን የጀመርነው ሰላማዊ ትግል ነው❗️
ይህን ስንጀምርም በሀገራችን ያለውን ጥያቄዎችን የማደባበስና ለመስማት ዝግጁ አለመሆንን በሚገባ ተረድተንና በማህበራዊ ሚዲያ ጩኸት ብቻ በመቅፅበት ለውጥ እንደማይመጣ ጠንቅቀን በማወቅና አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውም መስዕዋትነት ከፍለን ሙያችንን ነፃ ለማውጣትና ከአስከፊ የድህነት ኑሮ እንድንላቀቅ ነው።
ስለዚህም በዚህ የሰላማዊ ትግል ሂደት በመንግስት መበርገግና ስልጣንና ሀይልን እንደ አማራጭ በመውሰድ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የስም ማጥፋት፣ ደሞዝ መቀጣት፣ ከስራ መባረር፣ ማስፈራሪያ እና ዛቻ፣ ከሀላፊነት መነሳት፣ ድብደባ፣ እስር ብሎም እስከ ሞት ያሉ መስዋዕትነቶች ሊኖሩ ይችላሉ።
ነገር ግን ልብ በሉ ነገ የኛ ፀሀይ ትወጣለች፤ ከጥቂት የመከራና የችግር ቀናት አልያም ወራት በኋላ በአስከፊ የድህነት ደረጃ መኖራችን ያበቃል፤ ሙያችን የሚገባውን ክብር ያገኛል፤ ትውልድ ለት/ት የሚሰጠው ቦታ ይጨምራል፤ ህዝባችን በአዲሱ የጤና ስርዓት ለውጥ ከምንጊዜውም በበለጠ ሁኔታ የተሻለ ተጠቃሚ ይሆናል።
ስለሆነም ያለምንም ማወላወል እና ጊዜያዊ ችግሮችን ለትልቁ የትግላችን ምስል ሲባል እየተቋቋምን ከማዕከል የሚሰጠንን ትዕዛዝ ያለመሸራረፍ እንተግብር።
ማዕከላዊ ቦርዱ ያላሳወቀውንና ያልፈቀደውን ምንም አይነት ስብሰባ እና ውይይት ከመካፈል እንቆጠብ።
እኛ እራሳችንን አሳልፈን ለጋራ ጥቅማችን ስንል ሰጥተናልና በአንድነት ታዘዙን።
Internet የመዝጋት ሙከራ ሊኖር ይችላል። ከተዘጋ በእቅዳችን መሰረት ሙሉ ለሙሉ ስራ ለማቆም የምንገደድ ይሆናል። አፈናን በፍፁም አንታገስም‼️
አንድነታችን ጥንካሬያችን ሀይላችን‼️
የኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች ንቅናቄ ቦርድ
©️EHPM Board
አዲስ አበባ
ግንቦት 6, 2017 ዓ/ም
©️EHPM Board
አዲስ አበባ
ግንቦት 6, 2017 ዓ/ም