Healthcare workers preparing for second strike
Updates
00
D
:
00
H
:
00
M
:
00
S
⚠️ የመጨረሻውን ምዕራፍ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

⚠️ የመጨረሻውን ምዕራፍ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

May 12, 2025
⚠️ የመጨረሻውን ምዕራፍ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ
ሁሉም ባለሞያ እና የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚያውቀው ላለፉት 29 ቀናት ንቅናቄው በጥንቃቄ እንዲሁም ህጋዊና ጨዋነት በተሞላበት መንገድ ድህነታችንን እና ያለብንን ችግር የሚረዳ እና የሚመልስ መንግስት አለ ብሎ በማመን በቁጥር 12 የሚሆኑ የጤና ባለሞያውን አንገብጋቢ የህልውና ችግሮችን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በተዋረድ አስገብቶ መፍትሔ ሲጠባበቅ መቆየቱ ይታወቃል።
ይሁን እንጅ ምንም ተስፋ ሰጭ ባልሆነና መሬት ላይ ተፈፃሚ ያልሆነ አንድ መግለጫ ይሉት ቃለ ምልልስ ብቻ በመስጠት የተሰጡት 30 ቀናት መገባጀጃ ላይ እንገኛለን።
በገባነው ቃል መሰረት የተሰጡት ቀናት ሲያበቃ አገልግሎት መስጠት እንደምናቆም ንቅናቄው ደጋግሞ አስጠንቅቋል።
📌ጊዜውም ደረሰ እቅዳችንም ከነገ ማለትም ግንቦት 05/09/17 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ተፈፃሚ ይሆናል ብለን እናምናለን❗️
መንግስት ለህዝብ ምንም ደንታ እንደሌለው በመረዳት ሆስፒታሎችን እና ሌሎች የጤና ተቋማትን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ሊደርስ የሚችለውን የህዝባችንን እልቂት ለመቀነስ ድንገተኛ ክፍሎች ክፍት እንዲሆኑ ንቅናቄው ወስኗል።
📌ልብ በሉ እነዚህን ከፊል አገልግሎት የምንሰጠው የጊዜ ገደብ ከመንግሥት በሚሰጠን ምላሽ ላይ የተመረኮዘ ይሆናል።
በየትኛውም አካባቢ በባለሞያዎች ላይ እስር ፣ አካላዊ ጉዳት ማድረስ እና ማሳደድ የሚኖር ከሆነ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት ለማቋረጥ ልንገደድ እንደምንችል መንግሰት እና ውዱ ህዝባችን ሊገነዘብ ይገባል።
📌አጥጋቢ እና ተጨባጭ መልስ እስከሚሰጠን ድረስ በሚከተሉት የስራ ክፍሎች ብቻ አገልግሎት የምንሰጥ ሲሆን እነዚህም :-
✅የአዋቂ እና የህፃናት ድንገተኛ ክፍሎች
✅ የአዋቂና የህፃናት ፅኑ ህሙማን ክፍሎች
✅የማዋለጃ ክፍሎች ይሆናሉ።
📌በእነዚህ የህክምና ክፍሎች ለ1 ሳምንት የሚሆን ፕሮግራም ማውጣት ይጠበቅባቸዋል ።
📌 የስራ ጫናውን ለመቀነስ በቀጣይ ሳምንት አዲስ ፕሮግራም በማውጣት ተተኪ ባለሞያ ( በዚህ ሳምንት ቤቱ የነበረውን) ወደ ስራ ገበታ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
📌 ሌላው ባለሞያ በመኖሪያ ቤቱ ቁጭ ብሎ አንድነቱን እና ቁርጠኝነቱን ማሳየት ይጠበቅበታል።
📌 በማንኛውም ቀንና ሰዓት የንቅናቄው መሪዎች የሚሰጡትን መመሪያ ማየትና መተግበር አለበት።
📌 በባለሞያው ላይ ጥቆማና ወከባ የሚፈፅም ማንኛውንም አካል ባለሞያው ይመዝግብ ለንቅናቄው ሪፓርት ያድርግ።
የፀጥታ አካላት የሀይል አማራጭ የሚጠቀሙ ከሆነ ሀገሪቱ ወዳልተፈለገ ግጭት እንዳይገባ እና ሌላ አላማ ያላቸው አካላት እንዳይገቡ ጥንቃቄ ይደረግ።
ወደ ስራችን የሚመልሰን የጥያቄያችን ትክክለኛ ምላሽ እንጅ መሳሪያ ወይም የመንግስት ማስፈራሪያ አይደለም።
📌ውድ ባለሞያዎች እኛ (የንቅናቄው መሪዎች) እስከ ሞት ልንታገልላቹ እናንተ ትዕዛዝ መፈፀም እንዴት ጥርጣሬ ውስጥ ትገባላቹ?አታሳፍሩንም በዚህ እናምናለን ከድህነት የምንወጣበት በቀን 3ቴ የምንመገብበት ለኪራይ እና ቤተሰብ ለመጠየቅ ወይም ለመመስረት የማንሳቀቅበት ጊዜ ላይ ነን! እንበርታ❗️
ለቀጣዩ ትውልድ እና ለህዝባችን ጤና ስንል የጤና ስርዓቱን ማስተካከል የኛ ግዴታ ነው።
Only 15Hours Left ‼️
NOW OR NEVER‼️
የኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች ንቅናቄ
አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ
04/09/17 ዓ.ም