Healthcare workers preparing for second strike
Updates
00
D
:
00
H
:
00
M
:
00
S
የሰኞ መርሐ ግብሮች

የሰኞ መርሐ ግብሮች

May 12, 2025
1. ሁሉም ባለሙያ አጭር ውይይት በስራ ክፍሎቹ (department) ማድረግ እና አቋም መያዝ
2. ለአገልግሎት ክፍት በሚሆኑ ስራ ክፍሎች ሁሉንም ባለሙያ ያካተተ አዲስ የአንድ ሳምንት ፕሮግራም እንዲወጣ ማድረግ
3. የሴንትራል ትራያጅ (ማዕከላዊ ልየታ) ላይ የምትሰሩ ባለሙያወች እና አስተባባሪዎች የክፍሉን ቁልፍ ለሚመለከተው አካል ማስረከብ
4. የላብራቶሪ እና የፋርማሲ ባለሙያወች ሊበላሹ የሚችሉ የላብ ሪኤጀንቶች እና መድሀኒቶችን ወደ ሌሎች ተጓዳኝ ስራ ክፍሎች ማዛወር
5. ለአገልግሎት ዝግ በሚሆኑ ክፍሎች የምትሰሩ ባለሙያዎች ከማክሰኞ ጀምሮ አገልግሎት እንደማይኖር ለታካሚዎች(ለተገልጋዮች) ማስገንዘብ እና ለሌሎች እንዲያሳውቁ ማድረግ
6. ተገልጋይ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ባለሙያው በፍፁም ቀናነት እና ሰብዓዊነት ምላሽ መስጠት እና ማስረዳት
7. የታካሚን እንግልት ለማስቀረት ሲባል በየትኛውም ደረጃ ያላችሁ ጤና ተቋማት ከድንገተኛ ውጭ የሆኑ ሪፈሮችን ማስቀረት (ከታካሚው ጋር በመወያየት)
8. ለከተማው ነዋሪ ከተቻለ በበራሪ ፅሁፍ ካልተቻለ ቀጥተኛ ባልሆኑ መንገዶች አገልግሎት እንደሚቆም ማሳወቅ በተለይም ለጤና ተቋሙ የቦርድ አባል ለሆኑ የማህበረሰብ ተጠሪዎች ማሳወቅ።
9. ከማንኛውም አካል ጋር ወደ ግጭት ሊወስዱ የሚችሉ ሁኔታዎችን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግባቸው እና preventive measure ማስቀመጥ
10. የሚያዘናጉ እና የሰብዓዊነት ሸንጋይ ሁነው የሚመጡ እንዲሁም በየትኛውም ደረጃ ሀላፊዎች ለሚሰጥ መግለጫ፣ ደብዳቤ እንዲሁም ንግግሮች ጆሮ አለመስጠት።
📌 2ቀን ቀረው❗️
"ሀገራችን ድህነቷን አራግፋ በእድገት ጎዳና ላይ ናት ፤ ልጆቿ መራብ የለብንም።"
አንድነት ሀይል ነው‼️
የኢትዮጲያ ጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ