Healthcare workers preparing for second strike
Updates
00
D
:
00
H
:
00
M
:
00
S
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዶክተር ዳንኤል ፈንታነህ በዋስ ተፈታ፡፡ ‹‹ዶክተር ደቦል›› በሚል በስፋት የሚታወቀው ዶክተር ዳንኤል ፈንታነህ በባህር ዳር መታሰሩን ከዚህ ቀደም በዘ-ሐበሻ ዜና መዘገባችን ይታወሳል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዶክተር ዳንኤል ፈንታነህ በዋስ ተፈታ፡፡ ‹‹ዶክተር ደቦል›› በሚል በስፋት የሚታወቀው ዶክተር ዳንኤል ፈንታነህ በባህር ዳር መታሰሩን ከዚህ ቀደም በዘ-ሐበሻ ዜና መዘገባችን ይታወሳል፡፡

July 22, 2025
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዶክተር ዳንኤል ፈንታነህ በዋስ ተፈታ፡፡ ‹‹ዶክተር ደቦል›› በሚል በስፋት የሚታወቀው ዶክተር ዳንኤል ፈንታነህ በባህር ዳር መታሰሩን ከዚህ ቀደም በዘ-ሐበሻ ዜና መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በህክምና ላይ የሚያተኩሩ የተለያዩ መፅሀፍትን ያሳተመውና በጤና ባለሙያዎች መብት ንቅናቄ ላይ ንቁ ተሳታፊ የሆነው ዶክተር ዳንኤል በዛሬ እለት በ15 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር የተለቀቀ ሲሆን የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ይህንን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ የዶክተሩን መፈታት አዎንታዊ እርምጃ ካለው በኋላ ‹‹ማንኛውም ጤና ባለሙያ በሰላማዊ መንገድ መብቱን በመጠየቁ ወይንም ለጤና ስርአት ማሻሻያዎች በመሟገቱ ያለ ፍትህ የሚደረግ እስራትን እናወግዛለን›› ብሏል፡፡
ጨምሮም ‹‹የዶክተር ደቦል እስር በሙያችን ውስጥ ለፍትህ የሚታገሉ ሰዎች የሚያጋጥማቸውን ጭቆና አጉልቶ የሚያሳይ ነው›› ያለው ንቅናቄው ሲቀጥልም ‹‹መሰረታዊ መብቶችን መጠየቅ ወንጀል አይደለም፡፡ ለጤና ባለሙያዎ የህልውና ወሳኝ ጉዳዮች ወቅታዊና ተጨባጭ መፍትሄዎች ይገባቸዋል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ትርጉም ባለው መልስ እስከሚሟሉ ድረስ የጋራ ትግላችን ይቀጥላል›› በማለት አሳስቧል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ንቅናቄው ለጥያቄዎቹ መልስ እንዲሰጠው ጥሪ አቅርቦ መልስ ካልተሰጠው በመጪው መስከረም 5 ሁለተኛ ዙር የጤና ባለሙያዎች ስራ ማቆም አድማ እንደሚጠራ ማሳሰቡን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡