Healthcare workers preparing for second strike
Updates
00
D
:
00
H
:
00
M
:
00
S
We leave no health professional behind‼️

We leave no health professional behind‼️

June 26, 2025
የመጨረሻ አመት የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊቲ ሬዚደንት የሆነውን እና በ Debol Surgery መፅሀፍ፣ በMAC- Ethiopia መስራችነት፣ በ Dr Debol Facebook page ስለ ጤና ባለሞያዎች ህይወት መሻሻል እና ስለ ጤና ዘርፉ ለውጥ ግንዛቤ በመፍጠር እና ከዚያም በላይ በሚችለው መጠን በማስተባበር የታገለውን ዶ/ር ዳንኤልን ሀሰተኛ ታርጋ ለጥፎ ማሰር እና ለማሰቃየት መሞከር መላው የጤና ባለሞያውን መናቅ እና ጥያቄዎቻችንን ለመመለስ ዝግጁ አለመሆን ነው።
ለጤና ተማሪና ባለሙያው ገና የህክምና ተማሪ እያለ ጀምሮ በርካታ ስራዎችን የሰራው ተፅእኖ ፈጣሪው ወጣት የሙያ አጋራችንን ዶ/ር ዳንኤልን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቱት‼️
የኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች ንቅናቄ ቦርድ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነና ከተለያዩ ተፅእኖ ፈጣሪ ተቋማት እና ኢምባሲዎች ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ ማሳወቅ እንፈልጋለን። በቀጣይ ሁኔታውን አይተን የምንወስነውን ውሳኔ ተግባር ላይ ለማዋል ሁሉም ጤና ባለሙያ ዝግጁ እና ተባባሪ እንዲሆን እንጠይቃለን።
We leave no health professional behind‼️
#FreeDrDanielNow
#FreeTheDoctor
#EthiopianHealthProfessionalsUnderAttack
#WeNeedTangibleAnswersForOurLegitimateSurvivalQuestions
#StopArrestingHealthProfessionals